TPLF cannot be reformed. Like apartheid, it should be dismantled! - ETHIOMEDIA

የጀነራል ክንፈ ዳኘው ወንድም አቶ ኢሳያስ ዳኘው ዝርፊያ ሲጋለጥ

(አማኑአል አብነት) – EMF – ጋሽ ፖሊሱ ይህን መረጃ ለማግኘት በእርግጠኝነት 8 ወር ይጨርስብህ ነበር። እኔ ግን እንካ በነፃ ብየሀለሀ። አቶ ኢሳያስ ዳኘው፤ የሜይቴኩ አቶ ክንፈ ዳኘው ወንድም ነው፤ አማርኛም እንግሊዘኛም በቅጡ አይፈልጥም፣ በኢትዮ ቴሌኮም ውስጥ ትልቅ ስም ያለው በዝባዥ ነው። ይህ ሰው ከ2000ዓ.ም ጊዜ ጀምሮ በቀጣይ ጄነሬሽን ኔትወርክ(NGN)ፕሮጀክቶች ላይ አራጊ ፈጣሪ የነበረ ኤክስኪውቲቪ ነው። ከ1.5 billion USD telecom project ውስጥ የመንግስትን ካዘናን በvendor Finance ስም ያስበዘበዘ ጉማሬ ነው።

ከ2001-2004 ዓ.ም የኢትዮጵያ ቴሌኮሙኒኬሽን ኮርፖሬሽን የኔክስት ጀነሬሽን ኔትወርክ(NGN) እና የኔክስት ጀነሬሽን ፕሮግራም ኦፊስ(NGPO) ቢሮዎች ሲቋቋም ቀጥታ በእነ አቶ ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል የኢንፎርሜሽን እና ኮሚዩኒኬሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ትእዛዝ ከኢንተርፕራይዝ(የድርጅት)ስራ አስኪያጅነት ወደ ፕሮጀክት ማስተባበሪያ ፅ/ቤት ስራ አስኪያጅነት ተቀይሮ የ1.5billion Dollar project እመየራ ነበር። የኢትዮጵያ ቴሌኮሙኒኬሽን እያሰራ የነበረውን የ4.5 ቢሊዮን ዶላር ቬንደር(Vendor) ፕሮጀክት ከቻይናው ZTE ጋር የኢትዮጵያ ቴሌኮሙኒኬሽን እና የኢትዮጵያ መንግስት እንዲፈርሙ ከእነ ደብረፅዮን ጋር ካደረጉ ስዎች መካከል አንዱ ነው። ጨረታ ላይ ከETC ጋር የቀረቡት የቴሌኮም ካምፖኒዎች Nokia(ቀድሞ የኢትዮጵያን ቴሌኮም ኢንፍራስትራክቸር የሰራ)፣ Ericsson-የቴሌኮም እቃ አቅራቢ እና በጥራቱ የታወቀ ቬንደር እና service provider እና ZTE-ርካሽ እና ጥራታቸው በጣም ዝቅተኛ የሆነ እነዚህ ነበሩ። ያሸነፍ የነበረው እና ሁሉንም standard requisition ያሟላው ኤሪክሰን እና ኖክያ ነበር። ተመጣጣኝ ዋጋ አቅርቦ ያሸንፍ የነበረው ኤሪክሰን ነበር። ያው ከቻይናዎች ጋር በድርድር (lobby) ተደርጎ በጥቅም እና በወደቀ ኳሊቲ ከእነ ደብረፅዮን ትዕዛዝ እንዲገባ ተደረገ።

ቴሌኮሙኒኬሽን ኮርፖሬሽን ጥቅምት 2005 ዓ.ም ላይ ወደ ኢትዮ ቴሌኮም ሲቀየር ይህ ሰው የኢትዮ ቴሌኮም ቺፍ ኦፕሬሽን ኦፊሰር(COO) ሆነ ብዙ ፋዎሎችን ፈውሏል። ወይ አባ ግዶ ማንን ሊሰማ
1.ለድርጅት ደንበኞች የሚሰጥን የማስታወቂያ እና branding እቃዎችን ከፍላሽ እስከ ሞደም፣ከመደበኛ ስልክ እስከ ድብቅ ካሜራ ሀላል የሚዘርፍ ወንበዴ
2. ያለ ጨረታ ከሜይቴክ ለቴሌ ኬብል(ፋይበር እና ኮፕር)፣pvc ቱቦዎችን እና የመብራት ትራንስፎርመሮችን ፣የሰራተኛ እና መኪኖችን ተዋውሎ የሸጠ፣የሽያጭ ውሉን በውጭ ዶላር በዩክሬን ኩንባያ ስም ያስደለለ ጋንታ ዱርየ ነው። ደሞ ደሞዜ 8000 ብር ነው ይለናል፣የቴሌ ሹፌር እንኳን ከዛ በላይ ይበላል፤ይህን ሹፈት እና ሽሙጥ ክቡሩ ፍርድ ቤት ልደታ ከቴሌ ፋይናንስ ክፍል ያጣራ ወይም ከETA ኤግዚቢት ይያዝ
3.የወጭ ስልጠና በተለይ ህዋዊ እሱን የሚድምመው የለም የበረራ ገዞውን ማገላበጥ ይቻላል
4. ኢትዮ ቴሌኮም ያላገኘውን የሰው ሀይል እና የድርጅት አቅም በተገዙ የቻይና እና የእንግሊዝ ድርጅት የጥራት ለኪዎች አይሶ የማያሟላባቸውን እንደ ሽልማት በማስመሰል ድርጅቱን እንስዳስቀለደበት
5. በቴሌኮም ፍራውድ የወንድሙን ሜይቴክን እና ጓደኛውን የብሄራዊ ደህንትነን ተክለብርሀን እና ቢንምያን በመተማመን ከ12 ሚሊየን ዶላር በላይ ድርጅቱ ሲመዘበር ዝም ብሎ ያለፈ እና በድርጅቱ ሰራተኞች እና ደንበኞች ዋይታው ሰበዛ የሞደም አስተላላፊ አክተር ሆኖ መገኘቱ እና የጥቅም ተካፋይ መሆኑ
6. በአዳዲስ የV8 ክሩዘር ለአመራሮች መኪና ግዢ ላይ የአንበሳውን ድርሻ ወስዶ ያጭበረበረ እና በግዴታ ግዢው ሲፈፀም ኢትዮጵያ ውየጭ ምንዛሬ ችግር ውስጥ በገባችበት ሰአት ይገዛ ብሎ የፈቀደ የሀገር ክህደት የፈፀመ ዘራፊ ማፍያ ነው።
7. በዘሩ የሚመካ እና ለሌሎች ወንድም ዘሮች እና ኢትዮጵያውያን ደንታ የሌለው እንደውም በንቀት የተሞላ እብሪተኛ ነው።

ስላልተነገረ እንጅ ጉዱ እልፍ ነው። ደሞ ደሞዜ 8000 ብር ነው ይላል።
በሉ አስገቡልን አቦ ቤቱ ባልሳስሳት ኢምፔሪያ አካባቢ ነው። ለነገሩ አንድ 3 ቪላ ይኖረው ይሆናል ማን ያውቃል።

(Visited 437 times, 1 visits today)

You might be interested in